am_tn/2ki/15/17.md

1.6 KiB

የይሁዳ ንጉሥ ዓዛርያስ በነገሠ በሠላሳ ዘጠነኛው ዓመት

ይህ የአገዛዙ ሠላሳ ዘጠነኛው ዓመት እንደ ሆነ በግልጽ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ዓዛርያስ የይሁዳ ንጉሥ በሆነ በ39 ዓመት››

በያህዌ ዐይን ፊት ክፉ ነገር

የያህዌ፣ ዐይን የያህዌን ፍርድ ይወክላል፡፡ 2 ነገሥት 3፥2 ላይ ይህን እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በያህዌ ፍርድ ክፉ ነገር›› ወይም፣ ‹‹ያህዌ ክፉ የሚለውን››

ዘመኑንም ሁሉ

‹‹ዘመን›› የሚለው፣ ‹‹በኖረበት›› ተብሎ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በሕይወት በኖረበት ጊዜ ሁሉ››

ከናባጥ ልጅ ከኢዮርብዓም ኀጢአት አልተመለሰም

ከኀጢአት መራቅ ያንን ኀጢአት አለማድረግ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ዘካርያስ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ኀጢአት ማድረግን እንቢ አላለም›› ወይም፣ ‹‹የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ያደረገውን ኀጢአት አደረገ››

እስራኤልን ካሳተበት ኀጢአት

እዚህ ላይ ‹‹እስራኤል›› የሚለው ቃል፣ የእስራኤልን መንግሥት ሕዝብ ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የእስራኤል ሕዝብ ኀጢአት እንዲሠሩ ካደረገው››