am_tn/2ki/15/10.md

1.3 KiB

ሰሎም… ያቤስ

እነዚህ የሁለት ሰዎች ስም ናቸው፡፡

በዘካርያስ ላይ

‹‹በንጉሥ ዘካርያስ ላይ››

ኢብልዔም

ይህ የከተማ ስም ነው፡፡

በእግሩም ተተክቶ ነገሠ

ሰሎም በዘካርያስ ቦታ ንጉሥ ሆነ

በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ተመዝግቦአል

ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ተመዝግቦ ካለበት መጽሐፍ ማንበብ ትችላላችሁ፡፡››

ይህ የያህዌ ቃል ነበር

ቁጥር 10 ላይ የተነገሩት ሁኔዎታዎች የያህዌ ቃል ፍጻሜዎች ነበሩ ማለት ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ዘካርያስ ላይ የደረሰው በያህዌ ቃል መሠረት ነበር›› ወይም፣ ‹‹ዘካርያስ ላይ በደረሰው የያህዌ ቃል ተፈጸመ››

ልጆችህ እስከ አራት ትውልድ ድረስ በእስራኤል ዙፋን ላይ ይቀመጣሉ፡፡

ዙፋን ላይ መቀመጥ ንጉሥ መሆን ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ልጆችህ እስከ አራት ትውልድ ድረስ የእስራኤል ነገሥታት ይሆናሉ››