am_tn/2ki/15/08.md

2.2 KiB

ዓዛርያስ በነገሠ በሠላሳ ስምንተኛው ዓመት

ይህ የአገዛዙ ሠላሳ ስምንተኛው ዓመት መሆኑን ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የይሁዳ ንጉሥ ዓዛርያስ በነገሠ 38ኛው ዓመት››

የኢዮርብዓም ልጅ ዘካርያስ

ይህ ኢዮርብዓም በዚህ ስም የሚጠራ ሁለተኛው የእስራኤል ንጉሥ ነው፡፡ የንጉሥ ዮአስ ልጅ ነው፡፡

በሰማርያ ከተማ በእስራኤል ላይ ስድስት ወር ነገሠ

ሰማርያ የእስራኤል ንጉሥ በሆነ ጊዜ ንጉሥ ዘካርያስ የሚኖርባት ከተማ ነበረች፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በሰማርያ ሆኖ፣ በእስራኤል ላይ ስድስት ወር ነገሠ››

ክፉ አደረገ

‹‹ዘካርያስ ክፉ አደረገ››

በያህዌ ዐይን ፊት ክፉ አደረገ

የያህዌ ዐይን የሚወክለው የያህዌን ፍርድ ነው፡፡ 2 ነገሥት 3፥2 ላይ ይህን እንዴ እንደ ተረጐምኸው ተመለከት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በያህዌ ፍርድ ክፉ የሆነውን›› ወይም፣ ‹‹ያህዌ ክፉ የሚለውን››

ከናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ኀጢአት አልተመለሰም

ከኀጢአት መመለስ ያንን አለማድረግን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ዘካርያስ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓምን ኀጢአት ማድረግን እንቢ አላለም›› ወይም፣ ‹‹የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ያደረገውን ኀጢአት አደረገ››

የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም

ይህ ኢዮርብዓም የእስራኤልን መንግሥት ከመሠረቱ ዐሥሩ ሰሜናዊ ነገዶች የመጀመሪያው ንጉሥ ነበር፡፡

እስራኤልን ካሳተበት ኀጢአት

እዚህ ላይ ‹‹እስራኤል›› በእስራኤል መንግሥት ያለውን ሕዝብ ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የእስራኤልን ሕዝብ ካሳተበት ኀጢአት››