am_tn/2ki/15/06.md

1.2 KiB

በይሁዳ… የተጻፈ አይደለምን?

ይህ ጥያቄ የቀረበው ዓዛርያስን የሚመለከት መረጃ በዚህ ሌላ መጽሐፍ ውስጥ የሚገኝ መሆኑን ለአንባቢው ለማሳሰብ ነው፡፡ ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ 2 ነገሥት 8፥23 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በይሁዳ… ተጽፎአል›› ወይም፣ ‹‹በይሁዳ… ማንበብ ትችላላችሁ››

ዓዛርያስ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ

እንቅልፍ ሞትን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ዓዛርያስ እንደ አባቶቹ ሞተ›› ወይም፣ ‹‹እንደ አባቶቹ ዓዛርያስም ሞተ››

ከአባቶቹ ጋር ቀበሩት

‹‹ቤተ ሰቡ አባቶቹ በተቀበሩበት ቀበሩት››

በእግሩ ተተክቶ ነገሠ

‹‹በእግሩ ተተክቶ›› የሚለው ሐረግ፣ ‹‹በእርሱ ቦታ›› ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በዓዛርያስ ቦታ ንጉሥ ሆነ››