am_tn/2ki/15/04.md

1.3 KiB

በየኮረብታው ላይ ያሉት የማምለኪያ ስፍራዎች አልተወገዱም

ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ኮረብቶቹን ማንም አላስወገደም›› ወይም፣ ‹‹ዓዛርያስ ኮረብቶቹ እንዲወገዱ አላደረገም››

አልተወገደም

መወገድ ጨርሶ መደምሰስ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አልተደመሰሱም ነበር››

እስከሚሞትባት ቀን ድረስ

አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ››

ቤተ ሰቡን የሚያስተዳድረው የንጉሡ ልጅ ኢዮአታም ነበር

‹‹ቤተ ሰቡን›› የሚለውን በቤተ መንግሥቱ የሚኖሩ ሰዎችን ያመለክታል፡፡ ዓዛርያስ ለምጻም ስለ ነበር በተለየ ቤት መኖር ነበረበት፡፡ ልጁ ኢዮአታም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ፡፡

በቤቱ ሁሉ ኀላፊ ሆነ

በቤቱ ሁሉ ኀላፊ መሆን በቤቱ ላይ ባለ ሥልጣን መሆን ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በቤቱ ሁሉ ባለ ሥልጣን ሆነ›› ወይም፣ ‹‹በዓዛርያስ ቤተ መንግሥት ባለ ሥልጣን ሆነ››