am_tn/2ki/14/20.md

1.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ይህ የሆነው አሜስያስ ከሞተ በኃላ ነው፡፡

በፈረስ ተጭኖ አመጡት

‹‹የአሜስያስን ሬሳ በፈረስ ጭነው አመጡት››

የይሁዳ ሕዝብ በሙሉ ዕድሜው ዐሥራ ስድስት ዓመት የሆነውን ዓዛርያስን በአባቱ በአሜስያስ ፈንታ አነገሡት

ይህ አጠቃላይ አነጋገር ነው፡፡ አንዳንድ ንጉሥ መሆኑን የማይወዱ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የይሁዳ ሕዝብ ዐሥራ ስድስት ዓመት የሆነውን ዓዛርያስን በአባቱ በአሜስያስ ቦታ አነገሡት››

ኤላትን እንደ ገና የሠራ ዓዛርያስ ነበር

ዓዛርያስ ይህን ያደረገው ብቻውን አይደለም፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ኤላት እንድትሠራ ያዘዘ ዓዛርያስ ነበር›› ወይም፣ የኤላትን እንደ ገና መሠራት ሲቆጣጠር የነበሩ ዓዛርያስ ነበር››

ዓዛርያስ

በዚህ ዘመን ይህ ንጉሥ ይበልጥ የሚታወቀው፣ ‹‹ዖዝያን›› በተሰኘ ስሙ ነው፡፡

ኤላት

የይሁዳ ከተማ

ወደ ይሁዳ መለሳት

‹‹እንደ ገና ወደ ይሁዳ አመጣት››

ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ

ይህ ሞተ ለማለት ነው፡፡