am_tn/2ki/14/17.md

1.1 KiB

በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን?

ይህ ጥያቄ የቀረበው እነዚህ ሁሉ ተጽፈው ያሉ መሆኑን አንባቢውን ለማሳሰብ ነው፡፡ 2 ነገሥት 8፥23 ላይ ይህ ሐረግ እንዴት እንደ ተተረጐመ ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የይሁዳ ነገሥታት ታሪክ በተጻፈበት መጽሐፍ ተጽፈዋል››

አሜስያስ ላይ በኢየሩሳሌም አሤሩበት

ሤራ አንድ ሰው ወይም አንድ ነገር ላይ ጉዳት ለማድረስ በሚስጢር ማቀድ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በኢየሩሳሌም አንዳንድ ሰዎች አሜስያስ ላይ ተማከሩበት››

ለኪሶ

ይህ በደቡብ ምዕራብ ይሁዳ ያለ ከተማ ነው፡፡

እነርሱ ግን የሚከታተሉት ሰዎች ወደ ለኪሶ ላኩ

‹‹ሤራውን የጠነሰሱ ዎች አሜስያስን እንዲከታተሉ ሌሎች ሰዎች ወደ ለኪሶ ላኩ››