am_tn/2ki/14/08.md

2.3 KiB

አሜስያስ የኢዩ ልጅ፣ የኢዮአካዝ ልጅ ወደ ሆነው ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዮአስ፣ ‹‹ናና ፊት ለፊት ይዋጣልን›› ብሎ መልእክተኞች ላከበት

እዚህ ላይ፣ ‹‹ይዋጣልን›› የሚለው ሰራዊቱንም ይጨምራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከዚያም አሜስያስ፣ ‹‹መጥተህ ሰራዊቶቻችን ጦርነት ይግጠሙ›› በማለት ወደ ንጉሥ ኢዮአስ መልእክተኞች ላኩ››

የሊባኖስ ኩርንችት… ኩርንችቱን በእግሩ ረገጠው

ይህ የቃላት ስዕልና ዕንቆቅልሽ ነው፡፡ የሊባኖስ ዝግባ ትልቅ ሲሆን፣ ኩርንችት ደግሞ ትንሽና የማይረባ ነው፡፡ ኢዮአስ ራሱን ከሊባኖስ ዝግባ፣ አሜስያስን ከኩርንችት ጋር በማመሳሰል ጥቃት እንዳይሰነዝር አሜስያስን እያስጠነቀቀ ነው፡፡ በቋንቋህ ተመሳሳይ ንጽጽር ካለህ ልትጠቀምበት ትችላለህ፡፡

ኩርንቺት

እሾኻማ ቁጥቋጦ

ሴት ልጅህን ለልጄ በሚስትነት ስጠው

ይህን ቀጥተኛ ጥቅስ ቀጥተኛ ወዳልሆነ ጥቅስ መለወጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ዝግባው ሴት ልጁን ለኩርንቺቱ ወንድ ልጅ እንዲድርለት ጠየቀው››

በእርግጥ ኤዶምን ድል አድርገሃል

ይህ ኢዮአስ ለአሜስያስ የሰጠው ማስጠንቀቂያ ክፍል ነው፡፡ ‹‹አሜስያስ አንተ በእርግጥ ኤዶምን ድል አድርገሃል››

ልብህ አለመጠን አይኩራራ

ይህ ትዕቢትን የሚያመለክት የፈሊጥ አነጋገር ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ባደረግኸው ነገር በጣም ታብየሃል››

ድል በማድረግህ አትንጠራራ

‹‹ባገኘኸው ድል አትርካ››

የራስህን ውድቀት ለምን ትሻለህ?

ኢዮአስ ይህን የጠየቀው እርሱን እንዳያጠቃ አሜስያስን ለማስጠንቀቅ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ራስህ ላይ ሽንፈት የሚያመጣብህን ጠብ መጫር የለብህም››