am_tn/2ki/14/01.md

1.5 KiB
Raw Permalink Blame History

የእስራኤል ንጉሥ የኢዮአካዝ ልጅ ዮአስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት

‹‹የኢዮአካዝ ልጅ ዮአስ የእስራኤል ንጉሥ በሆነ በሁለተኛው ዓመት››

የኢዮአስ ልጅ አሜስያስ በይሁዳ መንገሥ ጀመረ

‹‹የኢዮአስ ልጅ አሜስያስ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ››

መንገሥ ሲጀምር ሃያ አምስት ዓመቱ ነበር፡፡

‹‹ንጉሥ ሲሆን 25 ዓመት ሆኖት ነበር››

በኢየሩሳሌም ተቀምጦ ሃያ ዘጠኝ ዓመት ገዛ

ለ29 ዓመት በኢየሩሌም ነግሦ ነበር››

ዮዓዳን

(ስሞች እንዴት እንደሚረጐሙ ተመልከት)

በያህዌ ፊት መልካም ነገር አደረገ፤ ግን እንደ አባቱ እንደ ዳዊት አልነበረም፡፡

‹‹የያህዌ ፊት›› የእርሱን ዐይን፣ የእርሱ ዐይን ደግሞ ፍርዱን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ኤሜስያስ በያህዌ ፊት ብዙ መልካም ነገሮች አደረገ፤ ሆኖም አባቱ ዳዊት ያደረገውን ያህል መልካም ነገሮች አላደረገም››

የአባቱን የዮአስን ፈለግ ተከተለ

ዮአስ ለያህዌ ታዘዙ መልካም ነገርንም አደረገ፤ ይህን የበለጠ ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አባቱ ዮአስ ያደረገውን መልካም ነገር አደረገ››