am_tn/2ki/13/22.md

1.5 KiB

ያህዌ ግን ራራላቸው፤ አዘነላቸው

ይህን ታሪክ በትንንሹ መከፋፈል ይጠቅማል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ ለእስራኤል ሕዝብ ስላዘነ ረዳቸው››

ስለዚህም ያህዌ አላጠፋቸውም

ያህዌ እስራኤልን ያላጠፋው ከኪዳኑ የተነሣ ነው፡፡ ይህን የበለጠ ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ ያላጠፋቸው በዚህ ምክንያት ነው›› ወይም፣ ‹‹ከኪዳኑ የተነሣ ያህዌ አላጠፋቸውም››

ከፊቱም አላስወገዳቸውም

የያህዌ ችላ ማለት እርሱ ካለበት ቦታ እስራኤልን በግልጽ ከመተው ጋር ተመሳስሎአል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አልተዋቸውም››

አዛሄል… ቤንሐዳድ… ዮአስ… ኢዮአካዝ

እነዚህ የነገሥታት ስሞች ናቸው

ዮአስ ሦስት ጊዜ ድል አደረገው

እዚህ ላይ ስለ ‹‹ዮአስ›› እና፣ ‹‹እርሱ የሚለው የሚያመለክተው ስለ ነገሥታቱና ስለ ሰራዊቱ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ዮአስ ሰራዊት የቤንሐዳድን ሰራዊት ሦስት ጊዜ ድል አደረገ››

የእስራኤልንም ከተሞች መልሶ ያዘ

‹‹ዮአስ ቤንሐዳድ ይዞአቸው የነበሩትን የእስራኤል ከተሞች ተቆጣጠረ››