am_tn/2ki/13/12.md

1.2 KiB

በይሁዳ ንጉሥ በአሜስያስ ላይ ያካሄደው ጦርነት

እዚህ ላይ፣ የዮአስ፣ ብርታት የእርሱ ጉልበት እንደ ሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከይሁዳ ንጉሥ አሜስያስ ሰራዊት ጋር ሲዋጋ የእርሱ ሠራዊት ያሳየው ኀይል››

በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን?

ጥያቄው የቀረበው ኢዮአስ ያደረገው ሁሉ በሌላ የታሪክ መጽሐፍ ተጽፎ የሚገኝ መሆኑን ለአንባቢው ማሳሰቢያ ለመስጠት ነው፡፡ 2 ነገሥት 1፥18 ይህ እንዴት እንደ ተተረጐመ ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የእስራኤል ነገሥታት ታሪክ በሚጻፍበት መጽሐፍ ተጽፎአል፡፡››

ዮአስ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ

ይህ ሞተ ማለት ነው፡፡

ኢዮርብዓም በዙፋኑ ተቀመጠ

እዚህ ላይ፣ ‹‹በዙፋን፣ መቀመጥ›› መንገሥ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከእርሱ በኃላ ኢዮርብዓም ነገሠ›› ወይም፣ ‹‹ቀጥሎ ኢዮርብዓም ነገሠ››