am_tn/2ki/13/10.md

1.5 KiB

በይሁዳ ንጉሥ በኢዮአስ ሰላሣ ሰባተኛው ዓመት

‹‹ዮአስ ይሁዳን ለ37 ዓመት ከገዛ በኃላ››

የኢዮአካዝ ልጅ ዮአስ በሰማርያ ከተማ እስራኤል ላይ መንገሥ ጀመረ

‹‹የኢዮአካዝ ልጅ ዮአስ በሰማርያ ሆኖ እስራኤልን መግዛት ጀመረ››

ዮአስ

ይህ የኢዮአካስ ልጅ የእስራኤል ንጉሥ ስም ነው፡፡

በያህዌ ፊት ክፉ ሥራ ሠራ

እዚህ ላይ፣ ‹‹ፊት›› የእግዚአብሔርን ሐሳብና ፍርድ ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ ክፉ ነው የሚለውን አደረገ››

የኢዮርብዓምን ኀጢአት ማድረግ አልተወም

ኀጢአትን ማቆም ኀጢአትን መተው እንደ ሆነ ተነግሯል፡፡ ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ዮአስ ኢዮርብዓም ሲያደርገው የነበረውን ኀጢአት ማድረጉን አልተወም›› ወይም፣ ‹‹ዮአስ የኢዮርብዓምን ኀጢአት ማድረጉን ቀጠለ››

እስራኤልን ካሳተበት ኀጢአት

‹‹ኢዮርብዓም እስራኤል እንዲበደል ካደረገበት››

በዚያው ገፋበት

ኀጢአት በኀጢአት መንገድ መሄድ እንደ ሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ዮአስ ይህንኑ ኀጢአት ማድረጉን ቀጠለ››