am_tn/2ki/13/06.md

1.1 KiB

ከኢዮርብዓም ቤት ኀጢአት አልተመለሱም

ኀጢአትን ማቆም ከኀጢአት መመለስ እንደ ሆነ ተናግሯል፡፡ ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፤ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እስራኤል ኢዮርብዓም ሲያደርግ የነበረውን ኀጢአት ማድረግ አልተወም›› ወይም፣ ‹‹እስራኤል ኢዮርብዓም ሲፈጽም የነበረውን ኀጢአት መፈጸም ቀጠለ››

የኢዮርብዓም ቤት

‹‹የኢዮርብዓም ቤተ ሰብ››

አጠፋቸው

‹‹የኢዮአካዝን ሰራዊት ድል አደረገ››

እንደ ዐውድማ ብናኝ አደረገው

የሶርያ ሰራዊት የእስራኤልን ሰራዊት ክፉኛ ድል አደረገ፤ የቀረውም በመከር ጊዜ ዐውድማ ላይ እንደሚረገጥ ብናኝ ጥቅም የለሽ ሆነ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በመከር ጊዜ ሠራተኞች በእግራቸው እንደሚያደቁት ገለባ ረገጣቸው››