am_tn/2ki/13/03.md

1.6 KiB

የያህዌ ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ

ያህዌ እስራኤልን መቆጣቱ ቁጣው የሚነድ እሳት እንደ ሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ በእስራኤል ላይ በጣም ተቆጣ››

የሶርያው ንጉሥ አዛሄልና ልጁ ቤንሐዳድ በነበሩበት ዘመን ሁሉ አሳልፎ በእጃቸው ሰጣቸው

እዚህ ላይ፣ ‹‹እነርሱ›› የሚለው የሚያመለክተው እስራኤልን ነው፤ ‹‹እጅ›› የሚለው እነርሱን የተቆጣጠረውን ኀይል ሥልጣን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሶርያ ንጉሥ አዛሄልና ልጁ ቤንሐዳድ በተደጋጋሚ እስራኤላውያንን በጦርነት ድል አደረጉ››

ያህዌን ለመነ

‹‹ወደ ያህዌ ጸለየ››

የሶርያ ንጉሥ እስራኤልን እንዴት አድርጐ እንዳስጨነቀ አይቶአል

እነዚህ ሁለት ሐረጐች የሚናገሩት ስለ አንድ ጉዳይ ሲሆን፣ የተደጋገሙት አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሶርያ ንጉሥ እስራኤልን በጣም ማስጨነቁን አዬ››

የሚታደጋቸው ሰው

‹‹የሚያድናቸው ሰው››

ከሶርያውያን ጭቁና (እጅ) ተላቀቁ

እዚህ ላይ፣ ‹‹እጅ›› እነርሱን የተቆጣጠረ ኀይልና ሥልጣን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከሶርያውያን ነጻ አወጣቸው››