am_tn/2ki/13/01.md

1.3 KiB

የይሁዳ ንጉሥ የአካዝያስ ልጅ ኢዮአስ በነገሠ በሃያ ሦስተኛው ዓመት

‹‹ኢዮአስ ይሁዳን ለ23 ዓመት ያህል ከገዛ በኃላ

በሰማርያ ከተማ በእስራኤል ላይ ነገሠ

‹‹በሰማርያ በሚገኘው የእስራኤል መንግሥት ገዛ››

ዐሥራ ሰባት ዓመት ገዛ

‹‹ኢዮአካዝ ለ17 ዓመት ንጉሥ ነበረ››

በያህዌ ፊት ክፉ ሥራ ሠራ

የያህዌ ፊት የያህዌን ፍርድና ሚዛን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በያህዌ ፍርድ ክፉ የሆነ›› ወይም፣ ‹‹ያህዌ ክፉ የሚለውን››

የኢዮርብዓምን ኀጢአት ተከተለ

‹‹ኢዮርብዓም የሚያደርገውን ኀጢአት አደረገ››

ኢዮአካዝ ከዚሁ ድርጊት አልተመለሰም

ኀጢአትን ማድረግ መተው ከእነርሱ መመለስ እንደ ሆነ ተነግሯል፡፡ ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ኢዮአካዝ የኢዮርብዓምን ኀጢአት ማድረጉን አልተወም›› ወይም፣ ‹‹ኢዮአካዝ የኢዮርብዓምን ኀጢአት ማድረጉን ቀጠለ››