am_tn/2ki/12/15.md

1.0 KiB

ለሠራተኞቹ እንዲከፍሉ ገንዘቡ የተሰጣቸው ላይ ተቆጣጣሪ ማድረግ አላስፈለጋቸውም

ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ገንዘቡን ተቀብለው ለዕድሳቱ ሠራተኞች የሚከፍሉ ሰዎች ላይ ተቆጣጣሪ ማድረግ አላስፈለገም››

ተጠያቂ መሆን

ምን ያህል ገንዘብ እንደ ተሰጠና እንደ ተከፈለ መዝገብ መያዝ

ስለ በደል መሥዋዕት ስለ ኀጢአት መሥዋዕት የሚቀርበው ገንዘብ ወደ ያህዌ ቤተ መቅደስ አይገባም ነበር

ገንዘቡ ለጥገናው ሥራ አይውልም ነበር፡፡ ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከበደል መሥዋዕትና ከኀጢአት መሥዋዕት የሚገኘው ገንዘብ ለያህዌ ቤተ መቅደስ ዕድሳት ሥራ ለሚደረግ ክፍያ አይውልም ነበር››