am_tn/2ki/12/01.md

1.3 KiB

ኢዩ በነገሠ በሰባተኛው ዓመት

‹‹ኢዩ በእስራኤል ላይ በነገሠ 7 ዓመት ሲሆነው››

ኢዮአስ መንገሥ ጀመረ

‹‹ኢዮአስ በይሁዳ ነገሠ››

ሳቢያ

‹‹ሳቢያ የተባለች የቤርሳቤህ ከተማ ተወላጅ››

በያህዌ ፊት መልካም ነገር አደረገ

ዐይን ማየትን፣ ማየት ደግሞ ሐሳብንና ፍርድን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ መልካም ነው የሚለውን›› ወይም፣ ‹‹ያህዌ መልካም ነው ብሎ የሚያስበውን››

ያስተምረው ነበር

‹‹ይመራው ነበር››

ከፍታ ቦታዎቹ ግን አልተወገዱም

ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፤ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሕዝቡ ግን ከፍታ ቦታዎቹን አላፈረሰም››

ሕዝቡ በከፍታዎቹ መሥዋዕት ያቀርብና ዕጣን ያጥን ነበር

በእነዚህ ቦታዎች እንዳያመልኩ ያህዌ ሕዝቡን ከልክሎ ነበር፡፡ ይህን የበለጠ ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹መሥዋዕት ለማቅረብና ዕጣን ለማጠን ሕዝቡ ያህዌ ወደማይፈልጋቸው ቦታዎች እየሄደ ነበር››