am_tn/2ki/11/19.md

1.6 KiB
Raw Permalink Blame History

አጠቃላይ መረጃ

አዲሱን ንጉሥ ኢዮአስን ከቤተ መቅደስ ወደ ቤተ መንግሥት ወሰዱት

የመቶ አለቆች

‹‹መቶ አለቆች›› የሚለው ሀረግ ምናልባት ወታደራዊ ሹመት ሊሆን ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጒሞች፣ 1) ‹‹መቶ›› የሚለው ቃል በእነዚህ ሹሞች ሥር ያለውን ወታደር ብዛት ሊያመለክት ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ የ100 ወታደሮች አዛዥ›› ወይም 2) ‹‹መቶ›› ተባሎ የተተረጐመው ቃል ወታደራዊ ምድብን እንጂ፣ ትክክለኛ ቁጥር የሚያመለክት አይደለም፡፡ አማራጭ ትርጉም፣ ‹‹ወታደራዊ ምድብ አዛዥ›› 2 ነገሥት 11፥4 ላይ ያለውን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡

ካራውያን

ይህ የቤተ መንግሥቱ ጠባቂዎች አንድ የተለየ ምድብ ነው፡፡

ንጉሡን ከያህዌ ቤተ መቅደስ አውጥተው ወደ ቤተ መንግሥት ሄዱ

‹‹ንጉሡን ከቤተ መቅደስ ወደ ቤተ መንግሥት አመጡት››

የአገሩም ሕዝብ ሁሉ ደስ አለው

ይህ አብዛኛው ለማለት ነው፣ ደስ ያላላቸው ሰዎችም እንደሚኖሩ ግልጽ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በአገሩ ያሉ ብዙ ሰዎች››

ከተማዪቱ ጸጥ አለች

‹‹ከተማዪቱ ተረጋጋች›› ወይም፣ ‹‹ከተማዪቱ ሰላማዊ ሆነች››