am_tn/2ki/11/04.md

1.6 KiB
Raw Permalink Blame History

አያያዥ ዐረፍተ ነገር

የንጉሥ አካዝያስ ልጆች ከተገደሉ በኃላ የንጉሥ አካዝያስ ልጅ ኢዮአስ ቤተ መቅደሱ ውስጥ ከተደበቀ በኃላ የተፈጸመውን ታሪክ ይቀጥላል፡፡

በሰባተኛውም ዓመት

‹‹በጐቶልያ አገዛዝ ሰባተኛው ዓመት›› ወይም፣ ‹‹ጐቶልያ ትገዛ በነበረበት 7ኛው ዓመት››

ዮዳሄ

ሊቀ ካህኑ

የመቶ አለቆች

ይህ የባለ ሥልጣኖች መጠሪያ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒሙ፣ 1) ‹‹መቶ›› የሚለው እነዚህ ባለ ሥልጣኖች ምን ያህል ወታደር ከእነርሱ ሥር እንደ ነበር በትክክል ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ የ100 ወታደሮች አዛዦች›› ወይም 2) ‹‹መቶ›› የሚለው ቃል በትክክል ቁጥርን የሚገልጽ ሳይሆን፣ የሚያመለክተው ሰራዊቱ ውስጥ ያለውን ምድብ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የወታደራዊ ምድብ አዛዦች››

ካራውያን

እነዚህ የተወሰኑ የቤተ መንግሥት ጠባቂዎች ቡድን ናቸው፡፡

ወደ ራሱ አመጣቸው

‹‹መጥተው እርሱን እንዲያገኙ አደረገ›› - እነዚህ ወታደሮች የሆነውን ነገር ቤተ መቅደስ ውስጥ ለሊቀ ካህኑ ለዮዳሄ ነገሩት፡፡

የንጉሡን ልጅ አሳያቸው

የንጉሥ አካዝያስ ልጅ ኢዮአስ በሕይወት መኖሩን ዮዳሄ ነገራቸው፡፡