am_tn/2ki/11/01.md

1.4 KiB

ጐቶልያ… ዮሳቤት… ኢዮአስ

እነዚህ የሰዎች ስሞች ናቸው

ልጇ መሞቱን በሰማች ጊዜ

‹‹ልጇ መሞቱን ባወቀች ጊዜ››

ተነሥታ የንጉሣዊ ቤተ ሰብ ልጆች ገደለች

ጐቶልያ ራሷ ልጆቹን አልገደለችም፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጐቶልያ ንጉሥ የሚሆኑ የአካዝያስ ቤተ ሰብ አባሎች እንዲገደሉ አገልጋዮቿን አዘዘች››

የአካዝያስን ልጅ ኢዮአስን ሊገድሉ ከነበሩት ልዑላን መካከል ሰርቃ ወሰደችው፡፡ እንዳይገድሉትም ከጐቶልያ በመደበቅ እርሱንና ሞግዚቱን በአንድ እልፍኝ ሸሸገቻቸው

‹‹የአካዝያስ ትንሹን ልጅ ኢዮአስን ወስዳ እርሱንና ሞግዚቱን ቤተ መቅደስ ባለው መኝታ ቤት ደበቀቻቸው ስለዚህ ሳይገደሉ ቀሩ››

ጐቶልያ አገሩ በምትገዛበት ጊዜም በያህዌ ቤት ተሸሸገ

ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ኢዮአስና ዮሳቤት ጐቶልያ አገሩን በምትገዛበት ዘመን ስድስት ዓመት በያህዌ ቤት ተደበቁ››

ምድር

ይህ በምድር የሚኖሩ ሰዎች ተለዋጭ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የይሁዳ ሕዝብ››