am_tn/2ki/10/34.md

1.1 KiB
Raw Permalink Blame History

በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን?

ይህን ጥያቄ በዐረፍተ ነገር ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ 2 ነገሥት 1፥18 ይህን ሐረግ እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ ተጽፎአል››

ኢዩ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ በሰማርያም ቀበሩት

ይህ ኢዩ ሞተ ማለት ነው፡፡ ከእነርሱ ጋር የተኛ ይመስል አባቶቹ በተቀበሩበት በታ መቀበሩን ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ኢዩ ሞተ፤ አባቶቹም በተቀበሩበት ቦታ በሰማርያ ተቀበረ››

ኢዮአካዝ

ይህ የሰው ስም ነው፡፡

ኢዩ በሰማርያ ተቀምጦ በእስራኤል ላይ የነገሠው ሃያ ስምንት ዓመት ነበር

‹‹ኢዩ ሰማርያ ሆኖ በእስራኤል ሃያ ስምንት ዓመት ነገሠ››

ሃያ ስምንት ዓመት

28 ዓመት››