am_tn/2ki/10/29.md

2.8 KiB
Raw Permalink Blame History

የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓምን ኀጢአት አልተወም

ይህ ማለት ኢዩ ኢዮርብዓም ያደርግ የነበረውን ኀጢአት እያደረገ ነበር ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ያደረገውን ኀጢአት ማድረጉን አልተወም››

ናባጥ

ከ2 ነገሥት 3፥3 የዚህን ሰው ስም እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡

የእስራኤል ኀጢአት

‹‹እስራኤል›› እዚያ የሚኖሩትን ሰዎች ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የእስራኤል ሕዝብ ኀጢአት››

ስላደረግህ

‹‹ስለ ፈጸምህ›› ወይም፣ ‹‹በማድረግህ››

በዐይኔ ፊት መልካም

ዐይን ማየትን፣ ማየት ደግሞ ሐሳብንና ፍርድን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹መልካም ነው ያልሁትን›› ወይም፣ ‹‹መልካም እንደ ሆነ ያሰብሁትን››

የአክዓብ ቤት

የአክዓብ፣ ‹‹ቤት›› የእርሱ፣ ‹‹ቤተ ሰብ›› ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የአክዓብ ቤተ ሰብ››

በልቤ ያለውን ሁሉ

እዚህ ላይ፣ ‹‹ልቤ›› - ‹‹ምኞትን›› ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንድታደርግ የምመኘው ሁሉ›› ወይም፣ ‹‹እንድታደርግ የምፈልገውን ሁሉ››

ዙፋን ላይ ይቀመጣል

ዙፋን ላይ መቀመጥ ንጉሥ መሆን ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ይነግሣል››

እስከ አራት ትውልድ

ይህ ልጁን፣ የልጅ ልጁን፣ አያቱንና ቅድመ አያቱን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ 4ኛ ትውልድ›› ወይም፣ ‹‹አራተኛ ትውልድ››

ኢዩ የያህዌን ሕግ ለመጠበቅ ጥንቃቄ አላደረገም

እዚህ ላይ፣ ‹‹መጠበቅ›› የሚያመለክተው፣ ‹‹መኖርን›› ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ኢዩ በያህዌ ሕግ መሠረት ለመኖር አልተጠነቀቀም››

በፍጹም ልቡ

እዚህ ላይ ‹‹ልብ›› የሰውን ፈቃድና ምኞት ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በሚያደርገው ሁሉ›› ወይም፣ ‹‹በሙሉ ፈቃደኝነት››

ከኢዮርብዓም ኀጢአት አልራቀም

ከአንድ ነገር ‹‹መራቅ›› ያንን ማድረግ ማቆም ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ኢዮርብዓም ባደረገበት መንገድ ኀጢአት ማድረጉን አልተወም››