am_tn/2ki/10/25.md

1.2 KiB

ለጠባቂዎቹና ለጦር አለቆቹ እንዲህ አለ

ምናልባት ኢዩ ለጠባቂዎቹ ከመናገሩ በፊት ከቤተ ጣዖቱ መውጣቱን መግለጽ ያስፈልገህ ይሆናል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከበአል ቤተ ጣዖት ወጥቶ ለጠባቂዎቹና ለጦር አለቆቹ እንዲህ አላቸው››

በሰይፍ

ሰዎቹ የበአልን አገልጋዮች የገደሉት በሰይፍ ነበር፡፡ ይህ ሐረግ የራሳቸውን ሰይፍ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በሰይፋቸው››

ወደ ውጭ አውጥታችሁ ጣሏቸው

ይህ ማለት የሞቱትን ሰዎች ከቤተ ጣዖቱ አውጥቶ መጣል ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሬሳቸውን ከቤተ ጣዖቱ አውጥታችሁ ጣሉ››

የኩስ መጣያ አደረገው

‹‹የሕዝብ ሽንት ቤት አደረገው››

እስከ ዛሬ ድረስ

ይህ ማለት ያ ነገር እስከ አሁን ድረስ አለ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከዚያ ወዲህ ሁሌም እንዲሁ ነው››