am_tn/2ki/10/15.md

1.2 KiB
Raw Permalink Blame History

የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ

ይህ የሰው ስም ነው፡፡

ልቤ ከአንተ ጋር እንደ ሆነ ልብህ ከእኔ ጋር ነውን?

እዚህ ላይ የሰው፣ ‹‹ልብ›› ታማኝነቱን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔ ለአንተ ታማኝ እንደ ሆንሁ ታማኝ ትሆንልኛለህን?

እንግዲያውስ እጅህን ስጠኝ

‹‹እንደዚያ ከሆነ እጅህን እጄ ላይ አስቀምጥ›› ወይም፣ ‹‹እንደዚያ ከሆነ፣ እንጨባበጥ›› በብዙ አገሮች ሁለት ሰዎች ከተጨባበጡ ስምምነታቸውን ያረጋግጣል፡፡

ያለኝን ቅናት እይልኝ

‹‹ቅናት›› የሚለው ቃል ቅጽልን ሊያመለክት ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ቀናተኛ መሆኔን እይልኝ››

ንጉሣዊ ዘር

‹‹ንጉሣዊ ቤተ ሰብን ሁሉ››

ለነቢዩ ለኤልያስ በተነገረው የያህዌ ቃል መሠረት

ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ የሰጠው ኤልያስ የተናገረው ትንቢት እንዲፈጸም››