am_tn/2ki/10/08.md

1.4 KiB
Raw Permalink Blame History

ከንጉሡ ልጆች

‹‹የአክዓብ ልጆች››

ኢዩ ወጥቶ ቆመ

‹‹ኢዩ ወደ ከተማው በር ወጥቶ ሰዎቹ ፊት ቆመ››

እናንተ ንጹሐን ናችሁ

ንጹህ የሆኑት ከምን እንደ ነበር መግለጽ ይቻላል፡፡ ምናልባትም 1)‹‹ኢዮራም ላይ በሆነው ንጹሐን ናችሁ›› ማለት ሊሆን ይችላል፡፡ ወይም 2) በኢዮራምና በቤተ ሰቡ ሞት ኃላፊነት የለባችሁም፡፡›› ‹‹ኢዮራምና ቤተ ሰቡ ላይ ከደረሰው እናንተ ንጹሐን ናችሁ›› ማለት ሊሆን ይችላል፡፡

እነሆ

ኢዩ ይህን ቃል የተጠቀመው ቀጥሎ ወደሚናገረው የሰዎቹን ትኩረት ለመሳብ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አድምጡ›› ወይም፣ ‹‹ቃሌን ስሙ››

እነዚህን ሁሉ ግን የፈጃቸው ማን ነው?

ኢዩ ይህን የጠየቀው ስለ ሁኔታው ሕዝቡ በጥልቀት እንዲያስቡ ለማድረግ ነው፡፡ ይህን በዐረፍተ ነገር መጻፍ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒሞቹም 1) ለ70ዎቹ የአክዓብ ልጆች ሞት ተጠያቂዎቹ የሰማርያ ሰዎች ናቸው›› 2) ‹‹እነዚህ ሰዎች እንዲሞቱ የያህዌ ፈቃድ ነበር››