am_tn/2ki/10/06.md

1.8 KiB

ደግሞ ጻፈላቸው

ኢዩራም አንድ ደብዳቤ ጽፎ ነበር፤ ይህ ሁለተኛው ነው አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንደ ገና ደብዳቤ ጻፈላቸው›› ወይም፣ ‹‹ሌላ ደብዳቤ ጻፈላቸው››

የእኔ ወገን ከሆናችሁ

‹‹የአንድ ሰው ወገን መሆን›› ለእርሱ ታማኝ መሆንና ደጋፊው መሆን ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለእኔ ታማኝ ከሆናችሁ››

ስሙ

ሰምታቸሁ ታዘዙ

ለቃሌ

የኢዩ፣ ‹‹ቃል›› እርሱ የተናገረውን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የምነግራችሁን››

ራሳቸውን ቆርጣችሁ… ወደ እኔ ኑ

የአክዓብን ልጆች ራሶች ቆርጠው ለኢዩ እንዲያመጡ ነው የተነገረው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ራሳቸውን ቆርጣችሁ አምጡልኝ››

የጌታችሁን ልጆች ራስ ቆርጣችሁ

ይህ የሚያመለክተው እነርሱን ገድሎ ራሳቸውን መቁረጥ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የጌታችሁን ልጆች ግደሉ፤ ራሳቸውንም ቁረጡ››

በቁጥር ሰባ… ሰባ ሰዎች

‹‹በቁጥር 70… 70 ሰዎች››

አሳዳጊዎቻቸው

ሲንከባከቧቸውና ሲያስተምሯቸው የነበሩ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሲያሳድጓቸው የነበሩ›› ወይም፣ ‹‹ሲንከባከቧቸው የነበሩ››

ወደ ኢዩ ላኳቸው

ይህ ማለት ቅርጫቶቹን ለኢዩ የሚያደርሱ ሰዎች ላኩ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ወደ ኢዩ የሚያደርሱ ሰዎች ላኩ››