am_tn/2ki/10/04.md

1.6 KiB

እነርሱ ግን እጅግ ፈርተው ነበር

‹‹በጣም ፈሩ››

ሁለት ነገሥታት

‹‹ሁለት ነገሥታት፣ ኢዮራምና አካዝያስ››

ኢዩ ፊት መቆም አልቻሉም

እዚህ ላይ፣ ‹‹መቆም›› ችግሩን መቋቋም ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ኢዩን መቋቋም አይችሉም›› ወይም፣ ‹‹ኢዩን መዋጋት አይችሉም››

እኛ እንዴት ልንቋቋመው እንችላለን?

ሰዎቹ ይህን ያሉት ኢዩን እንደማይችሉት ለመናገር ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኛም ብንሆን እርሱን መቋቋም አንችልም›› ወይም፣ ‹‹እኛም አንችለውም››

የከተማዪቱ ገዥ

‹‹የከተማዪቱ ከንቲባ›› እዚህ ላይ፣ ‹‹ገዥ›› ሥልጣንና ኀላፊነት ያለው ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በከተማዋ ላይ ኀላፊ የነበረው ሰው››

የልጆቹ ሞግዚቶች

ይህ ማለት የንጉሡን ልጆች ያሳደጉ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የንጉሡን ልጆች ያሳደጉ››

በዐይንህ ፊት ደስ የሚያሰኝህን አድርግ

እዚህ ላይ፣ የኢዩ፣ ‹‹ዐይን›› የእርሱን፣ ‹‹ፊት›› ያመለክታል፤ የእርሱ ፊት እርሱ የሚያስበውን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ትክክል የመሰለህን አድርግ›› ወይም፣ ‹‹መልካም መስሎ የታየህን አድርግ››