am_tn/2ki/09/35.md

1.4 KiB

ሌላ ያገኙት አልነበረም

‹‹ከአካሏ የቀረ አልነበረም›› ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያገኙት ከአካሏ የተረፈ››

ከእጇ መዳፍ በቀር

መዳፍ የእጅ ውስጥ ክፍል ነው፡፡

ቴስቢያዊው

ይህ ከቴስቢ የሆነ ሰው ማለት ነው፡፡ 2 ነገሥት 1፥3 ላይ ይህን እንዴት እንደተረጐምኸው ተመልከት፡፡

የኤልዛቤል ሥጋ እርሻ ውስጥ እንደ ፍግ ስለሚሆን ማንም ይህች ኤልዛቤል ናት አይልም

ይህ ፍግ እርሻ ውስጥ እንደሚበታተን የኤልዛቤልም ሥጋ ቁርጥራጭ እርሻ ውስጥ መበታተኑን ይናገራል፡፡ ሥጋዋ በጣም ስለሚበጣጠስ ማንም ሰብሰቦ መቅበር አይችልም፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የኤልዛቤል ሥጋ እንደ ፍግ እርሻ ውስጥ ይበታተናል… ስለዚህ እርሷ መሆንዋን ማንም ማወቅ አይችልም››

ፍግ

ለማዳበሪያ የሚውል ነገር

ማንም፣ ‹‹ይህች ኤልዛቤል ናት›› ሊል አይችልም

‹‹ማንም እርሷ መሆንዋን አያውቅም›› ወይም፣ ‹‹ማንም ኤልዛቤል ናት ብሎ መናገር አይችልም››