am_tn/2ki/09/30.md

1.2 KiB

ዐይኗን ተኳኩላ፤ ጠጉራንም አሰማምራ

‹‹ዐይኗን ተኳኩላ፣ ጠጉርዋን ተሠርታ››

ጌታህን የገደልህ አንተ ዘምሪ የመጣኸው በሰላም ነውን?

ኤልዛቤል ይህን የጠየቀችው ኢዩ የመጣው በሰላም እንዳልሆነ ለማመልከት ነው፡፡ ይህን በዐረፍተ ነገር መጻፍ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አንተ ጌታህን የገደልህ ዘምሪ፣ የመጣኸው ለሰላም አይደለም››

ጌታህን የገደልህ አንተ ዘምሪ

እዚህ ላይ ኤልዛቤል፣ ‹‹ዘምሪ›› ያለችው ነፍሰ ገዳይ መሆኑን ለማመልከት ነው፡፡ ዘምሪ ንጉሥ መሆን ስለ ፈለገ፣ የእስራኤልን ንጉሥ የገደለ የጦር አዛዥ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ዘምሪ ጌታውን እንደ ገደለ አንተም ጌታህን የገደልህ››

ዘምሪ

ይህ የሰው ስም ነው፡፡

አብሮኝ ያለ ማነው?

‹‹አብሮ መሆን›› ታማኝና ተባባሪ መሆን ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለእኔ ታማኝ የሆነ››