am_tn/2ki/09/25.md

1.1 KiB

ቢድቃር

ይህ የሰው ስም ነው፡፡

አንሣውና ጣለው

‹‹ሬሳውን አንሥተህ ጣል›› ወይም፣ ‹‹በድኑን አንሣና ጣል››

አስታውስ

‹‹አትርሳ››

አባቱን አክዓብን

ይህ ማለት የጋለቡት ከአክዓብ ሰረገላ ተከትለው ነበር ማለት ነው፡፡

የናቡቴንና የልጆቹን ደም

እዚህ ላይ፣ ‹‹ደም›› የሚያመለክተው ግድያን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የናቡቴንና የልጆቹን መገደል››

እንድትከፍል አደርግሃለሁ

ይህ ማለት ለፈጸመው ክፉ ነገር ለአክዓብ ተገቢ ቅጣት ይሰጣል ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ላደረግኸው ክፉ ነገር የሚገባህን እሰጥሃለሁ››

አንሣውና በዚሁ እርሻ ውስጥ ጣለው

‹‹ሬሳውን አንሥተህ ናቡቴ እርሻ ውስጥ ጣለው››

በያህዌ ቃል መሠረት

‹‹የተነገረን ትንቢት እንዲፈጸም››