am_tn/2ki/09/19.md

1.1 KiB

ስለዚህ ንጉሡ ሌላ ፈረሰኛ ላከ

‹‹ስለዚህ ንጉሥ ኢዮራም ከኢዩና ከሰራዊቱ ጋር እንዲገናኝ ሁለተኛ ፈረሰኛ ላከ፡፡››

ሁለተኛ ሰው

ቀደም ሲል ኢዮራም አንድ ሰው ልኮ ነበር፡፡ ይኸኛው ቀጣዩ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሌላ ሰው››

ከሰላም ጋር ምን ጉዳይ አለህ?

ኢዩ ይህን ጥያቄ ያቀረበው የመጣው ለሰላም ቢሆን ወይም ባይሆን፣ ያ የእርሱ ጉዳይ አለመሆኑን ለመልእክተኛው ለመንገር ነው፡፡ ይህን በዐረፍተ ነገር መጻፍ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለሰላም መምጣት አለመምጣቴ የአንተ ጉዳይ አይደለም››

ሠረገላ አነዳዱ ልክ እንደ ናሜሲ ልጅ እንደ ኢዩ አነዳድ ነው

ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሠረገላው ነጂ አነዳድ የኖሜሲ ልጅ የኢዩን አነዳድ ይመስላል››