am_tn/2ki/09/14.md

2.7 KiB

ናሜሲ

የዚህን ሰው ስም 2 ነገሥት 9፥2 እንደ ተረጐምህ ተርጒመው፡፡

አሁን ኢዮራም

ይህ ቃል እዚህ ጥቅም ላይ የዋለው የዋናውን ታሪክ ፍሰት ገታ ለማድረግ ነው፡፡ ኢዮራም እንዴት እንደ ቆሰለና ለማገገም ወደ ኢይዝራኤል እንደ ሄደ ጸሐፊው የታሪኩን ዳራ መረጃ ያቀርባል፡፡

እስራኤል ሁሉ

ይህ የሚያመለክተው የእስራኤልን ሰራዊት ብቻ እንጂ፣ በእስራኤል የሚኖረውን ሁሉ አይደለም፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እርሱና ሰራዊቱ›› ወይም፣ ‹‹እርሱና የእስራኤል ሰራዊት››

ለማገገም

ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ቁስሉ እንዲሻለው››

ሶርያውያን ካደረሱበት ቁስል

ይህ ማለት የቆሰለው ከሶርያውያን ጋር ሲዋጋ ነበር ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከሶርያ ሰራዊት ጋር ሲዋጋ ኢዮራም ከደረሰበት ቁስል››

በሶርያ ንጉሥ አዛሄል ላይ

ይህ የሚያመለክተው አዛሄልና ሰራዊቱን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በሶርያ ንጉሥ በአዛሄልና በሰራዊቱ››

አዛሄል

የዚህን ሰው ስም 2 ነገሥት 8፥8 ላይ እንደ ተረጐምኸው ተርጉመው፡፡

ኢዩ ለኢዮራም አገልጋዮች እንዲህ ከሆነ

ይህ የሚናገረው ከኢዮራም ጋር በሬማት ዘገለዓድ ስለ ነበሩት ባለ ሥልጣኖች ነው፡፡

እንግዲህ ሐሳባችሁ እንዲህ ሆነ

‹‹ከእኔ ጋር የምትስማሙ ከሆነ›› ኢዩ ይህን ያለው ንጉሥ ለመሆንና ያለውን ሐሳብ ሕዝቡ ይደግፉ እንደ ሆነ ለማመልከት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በእውነት ንጉሣችሁ እንድሆን የምትፈልጉ ከሆነ››

ይህን ነገር ወደ ኢይዝራኤል ሄዶ እንዳይናገር

ይህ የሚያመለክተው የኢዩን ዕቅድ ለኢዮራምና ለሰራዊት መናገርን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በኢይዝራኤል ያለውን ንጉሥ ኢዮራምና ሰራዊቱን ለማስጠንቀቅ››

አሁን አካዝያስ

እዚህ ላይ፣ ‹‹አሁን›› የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው የዋናውን ታሪክ ፍሰት ገታ ለማድረግ ነው፡፡ እዚህ ላይ ጸሐፊው አካዝያስ ኢዮራምን ስለ ጐበኘበት ምክንያት ዳራ የሚሆን መረጃ ይሰጣል፡፡