am_tn/2ki/09/11.md

1.5 KiB

የጌታው አገልጋዮች

ይህ ንጉሥ አክዓብን የሚያገለግሉ ሌሎች ባለ ሥልጣኖች ያመለክታል፡፡

ይህ እብድ

‹‹ወፈፌ ሰው››

ሰውየውንም ሆነ የሚናገረውን ታውቃላችሁ

ኢዩ እርሱ ወጣት ነቢይ እንደ ሆነና ወጣት ነቢያት ደግሞ በአጠቃላይ ስለሚናገሩት ነገር ሁሉም እንደሚያውቁ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንደ እርሱ ያሉ ወጣት ነቢያት የሚናገሩትን ታውቃላችሁ››

ንገረን

‹‹እርሱ ያለውን ንገረን››

እንዲህና እንዲህ አለኝ

‹‹ስለ ተለያዩ ነገሮች ነገረኝ››

ልብሳቸውን እያወለቁ በሚራመድበት ደረጃ ላይ አነጠፉ

በዚህ ባሕል መሠረት እግሮቹ ቆሻሻውን መሬት እንዳይረግጡ ልብሶችን አውልቆ እግር ሥር ማንጠፍ ለንጉሡ ያላቸውን ክብር መግለጫ መንገድ ነበር፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከላይ ያለውን ልብሳቸውን እያወለቁ እንዲራመድበት ኢዩ ፊት አኖሩ››

መለከትም ነፍተው እንዲህ አሉ

ሁሉም ሰው መለከት አይነፋም፡፡ መለከት የሚነፋው አንድ ሰው ብቻ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከእነርሱ አንዱ መለከት ነፍቶ እንዲህ አለ››