am_tn/2ki/09/09.md

1.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ወጣቱ ነቢይ የእስራኤል ንጉሥ እንዲሆን ለቀባው ለኢዩ የያህዌን ቃል መናገሩን ቀጥሏል፡፡

የአክዓብን ቤት እንደ… አደርጋለሁ

ይህ ማለት ኢዮሮብዓምን ባኦስንና ቤተ ሰቡን እንዳጠፉ ሁሉ ያህዌ አክዓብንና ቤተ ሰቡን ያጠፋል ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹… እንዳስወገድሁ የአክዓብንም ቤት አስወግዳለሁ››

ቤት

ይህ ቃል ሦስት ጊዜ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በእያንዳንዱ ጊዜ፣ ‹‹ቤት የሚለው ስሙ የተጠቀሰው ሰው፣ ‹‹ቤተሰብ›› ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የ… ቤተ ሰብ››

ናባጥ… አኪያም

እነዚህ የሰው ስሞች ናቸው፡፡ ናባጥ የሚለውን ስም 2 ነገሥት 3፥3 ላይ ያለውን እንደ ተረጐምህ ተርጉመው፡፡

ኤልዛቤልን… ውሾች ይበሏታል፡፡

ይህ ማለት የሞተ አካሏን ውሾች ይበሉታል ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የኤልዛቤልን ሬሳ ውሾች ይበሉታል››