am_tn/2ki/08/28.md

1.0 KiB

አካዝያስ ከአክዓብ ልጅ ከኢዮራም ጋር ሆኖ የሶርያ ንጉሥ አዛሄል ላይ ዘመተ

እዚህ ላይ የተጠቀሰው የሦስት ነገሥታት ስም አብረዋቸው ያሉ ሰራዊቶችንም ይመለከታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የአካዝያስ ሰራዊት፣ የሶርያ ንጉሥ አዛሄልን ለመውጋት ከእስራኤል ንጉሥ ኢዮራም ሰራዊት ጋር ተባበረ››

ለማገገም

ይህን፣ ‹‹እንዲፈወስ›› ወይም፣ ‹‹እንዲሻለው›› በማለት መተርጐም ይቻላል፡፡

የሶርያ ንጉሥ አዛሄል ላይ

‹‹አዛሄል›› የሚለው ራሱንና ሰራዊቱን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሶርያ ንጉሥ አዛሄል ሰራዊት››

ኢዮራም ቆስሎ ነበር

ይህን በሌላ መልኩ መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሶርያውያን ኢዮራምን አቁስለውት ነበር››