am_tn/2ki/08/22.md

2.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ

የይሁዳ ንጉሥ ኢዮራም ሞተ፤ ልጁ አካዝያስ ነገሠ

ኤዶም እስከ ዛሬ ድረስ በይሁዳ ላይ እንደ ዐመፀ ነው

ከዚያ በኃላ ኤዶም በይሁዳ ቁጥጥር ሥር አልሆነም፤ እስከ ዛሬም እንደዚያው ነው››

በይሁዳ ላይ

‹‹ይሁዳ›› የይሁዳን ንጉሥ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በይሁዳ ንጉሥ ላይ›› ወይም፣ ‹‹በይሁዳ ንጉሥ ሥልጣን ላይ››

እስከ ዛሬ ድረስ

ይህ እስከ ተጻፈ ድረስ

ልብናም በዚሁ ጊዜ ዐምፆ ነበር

እንደ ኤዶም ሁሉ ልብና በይሁዳ ንጉሥ ላይ ዐመፀ፡፡ ‹‹ልብና›› እዚያ የሚኖሩትን ሰዎች ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የልብና ሕዝብ››

በኢዮራም ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ነገር

‹‹ስለ ኢዮራም ታሪክና ያደረገውን ለማንበብ››

በይሁዳ… ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን?

ጥያቄው የቀረበው ኢዮራምን የሚመለከት መረጃ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ እንደሚገኝ ለአንባቢ ለመንገር ወይም ለማሳሰብ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እነዚህ ነገሮች በይሁዳ… ተጽፈዋል›› ወይም፣ ‹‹ስለዚያ ሁሉ በይሁዳ… ተጽፎአል››

ኢዮራም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ ከእነርሱም ጋር ተቀበረ

‹‹አንቀላፋ›› ማለት ‹‹ሞተ›› የሚለው ሌላ ቃል ነው፡፡ ከሞተ በኃላ አባቶቹ በተቀበሩበት መቃብር ተቀበረ፡፡ ‹‹ተቀበረ›› የሚለውን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ኢዮራም እንደ አባቶቹ አንቀላፋ፤ ከአባቶቹም ጋር ቀበሩት››

ልጁ አካዝያስም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ

‹‹ከዚያም የኢዮራም ልጅ አካዝያስ ነገሠ››