am_tn/2ki/08/10.md

1.7 KiB

እስኪያፍር ድረስ

‹‹አዛሄል ምቾት እስኪያጣ ድረስ››

ጌታዬ

አዛሄል ኤልሳዕን እንዲህ ያለው እርሱን ለማክበር ነው፡፡

ስለማውቅ ነው

እግዚአብሔር ለኤልሳዕ ወደ ፊት የሚሆነውን አሳይቶታል፡፡

አንተ የምታደርገውን

አንተ የሚለው የሚወክለው አዛሄልን ቢሆንም፣ እዚህ ላይ ግን ወደ ፊት ንጉሥ ሲሆን በእርሱ ሥር የሚሆኑትን ወታደሮች ነው፡፡

ታቃጥላለህ… ትገድላለህ

‹‹አንተ›› የሚለው የሚወክለው አዛሄልን ቢሆንም፣ እዚህ ላይ የሚያመለክተው አዛሄልን ሳይሆን ወታደሮቹን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ወታደሮችህ ያቃጥላሉ… ወታደሮችህ ይገድላሉ››

ሕፃናታቸውንም በምድር ላይ ትፈጠፍጣለህ

‹‹ትንንሽ ልጆቻቸውን ትጨፈልቃለህ›› — ይህ ልጆቹን የሚገድሉ ወታደሮችን ጭካኔ ያመለክታል፡፡

ጐልማሶቻቸውን በሰይፍ ትገድላለህ

ይህ ማለት ሰዎቹ በጦርነት ይገደላሉ ማለት ነው፡፡ ሰይፍ በጦርነት ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውል ዋና መሣሪያ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በጦርነት ሰዎቻቸውን በሰይፍ ትገድላለህ››

ያረገዙ ሴቶቻቸውን ሆድ ትቀድዳለህ

ይህ ለይቶ የሚያመክተው የማሕፀን መቀደድን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያረገዙ ሴቶቻቸውን ማሕፀን በሰይፍ ትቀድዳለህ››