am_tn/2ki/07/16.md

2.1 KiB
Raw Permalink Blame History

ሰፈሩን በዘበዙ

ይህ ከተሸነፈው ሰራዊት ንብረት መውሰድ ማለት ነው፡፡

ስለዚህ አንድ መስፈሪ ማለፊያ ዱቄት በአንድ ሰቅል፣ ሁለት መስፈሪያ ገብስም በአንድ ሰቅል ተሸጠ

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ስለዚህም ሰዎቹ አንዱን መስፈሪያ ማለፊያ ዱቄት በአንድ ሰቅል፣ ሁለቱን መስፈሪያ ገብስም በአንድ ሰቅል ሸጡ››

አንድ መስፈሪያ ማለፊያ ዱቄት… ሁለት መስፈሪያ ገብስ

እዚህ ላይ፣ ‹‹መስፈሪያ›› ተብሎ የተተረጐመው፣ ‹‹ሴህ›› የሚለው ቃል ሲሆን፣ ደረቅ ነገሮች በሚለኩበት መለኪያ ከ7 ሊትር ጋር እኩል ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ 7 ሊትር ማለፊያ ዱቄት… 14 ሊትር ገብስ››

ሰቅል

ሰቅል ከ11 ግራም ጋር የሚተካከል መለኪያ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ 11 ግራም የሚያህል ብር›› ወይም፣ ‹‹አንድ የብር ሳንቲም››

የያህዌ ቃል እንደ ተናገረው

እዚህ ላይ፣ ‹‹ቃል›› ያህዌን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ እንደ ተናገረው››

ንጉሡ እጁን ይደገፈው የነበረው የጦር አለቃ

የንጉሡ የቅርብ ረዳት የነበረው ከፍተኛ ባለ ሥልጣን ንጉሡ እጁን ይደግፈው የነበረ ሰው እንደ ሆነ ተነግሮአል 2 ነገሥት 7፥2 ላይ ያለውን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለንጉሡ ቅርብ የነበረው የጦር አዛዥ›› ወይም፣ ‹‹የንጉሡ የቅርብ ረዳት የነበረው የጦር አዛዥ

ሕዝቡ ሲጋፋ ረጋገጠው

ሕዝቡ ምግብ ለማግኘት እየተጣደፉ ስለ ነበር፣ ሰውየው ጋር ተጋጩ፤ ረጋግጠውም ገደሉት፡፡