am_tn/2ki/06/32.md

3.6 KiB
Raw Permalink Blame History

ንጉሡም መልእክተኛ ቀድሞት እንዲሄድ አደረገ

‹‹ከንጉሡ ፊት›› ማለት ከአገልጋዮቹ አንዱ መሆን ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የእስራኤል ንጉሥ ከአገልጋዮቹ አንዱን እንደ መልእክተኛ ላከ››

የተላከውም ሰው ከመድረሱ በፊት ኤልሳዕ ለሽማግሌዎቹ

እዚህ ላይ ኤልሳዕ የንጉሡ መልእክተኞች ከመምጣታቸው በፊት ለሽማግሌዎቹ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹መልእክተኛው ከመድረሱ በፊት ኤልሳዕ ለሽማግሌዎች እንዲህ አለ››

ይህ ነፍሰ ገዳይ ራሴን ለመቁረጥ ሰው መላኩን ታያላችሁ?

እዚህ ላይ ኤልሳዕ ይህን የጠየቀው ወደ ንጉሡ መልእክተኛ ትኩረት ለመሳብና ንጉሡን ለመዝለፍ ነው፡፡ ይህን በዐረፍተ ነገር መጻፍ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ይህ የነፍሰ ገዳይ ልጅ ራሴን የሚቆርጥ ሰው መላኩን ተመልከቱ››

የነፍሰ ገዳይ ልጅ

ይህም ማለት የእስራኤል ንጉሥ የነፍስ ገዳይ ባሕርይ ነበረው ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ይህ ነፍሰ ገዳይ›› ወይም፣ ‹‹ያ ነፍሰ ገዳይ››

መላኩን

አንድ ሰው መላኩ ግልጽ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለ… ሰው ልኳል››

ራሴን ለመቁረጥ

ይህ መሰየፍ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ራሴን ቆርጦ ለመጣል›› ወይም፣ ‹‹ራሴን ለመሰየፍ››

እነሆ አሁንም

እዚህ ላይ ኤልሳዕ በዚህ ቃል የተጠቀመው ቀጥሎ ለሚናገረው የሽማግሌዎቹን ትኩረት ለመሳብ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንድታደርጉ የምፈልገውን ስሙ››

በሩን ዘግታችሁ እንዳይገባ አድርጉ

በተዘጋ በር ማንም መግባት አይችልም፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ወደ ውስጥ እንዳይገባ በሩን ዝጉ››

የጌታው እግር ኮቴ ከኃላው ይሰማ የለምን?

ኤልሳዕ ይህን ለሽማግሌዎቹ የተናገረው ንጉሡ ከኃላው እየመጣ መሆኑን በእርግጠኝነት ለመናገር ነው፡፡ ይህን በዐረፍተ ነገር መጻፍ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የጌታው እግር ኮቴ ድምፅ ከኃላው ነው›› ወይም፣ ‹‹እርሱ ከደረሰ በኃላ ንጉሡም ወዲያው ይመጣል››

እነሆ መልእክተኛው

‹‹የምነግራችሁ ነገር እውነትና አስፈላጊ ስለሆነ ልብ በሉ››

ይህ ጥፋት

‹‹በእርግጥ ይህ ጥፋት›› እዚህ ላይ፣ ‹‹እነሆ›› ለሚከተለው አጽንዖት ይሰጣል፡፡ ‹‹ይህ ጥፋት›› የሚለው ሐረግ በሰማርያ የሚመጣውን ራብና የሚያስከትለውን ችግር ያመለክታል፡፡

ታዲያ፣ እኔ ከእግዚአብሔር ምን እጠብቃለሁ?

ንጉሡ ይህን የጠየቀው ያህዌ ይረዳናል ብሎ እንደማያምን አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ ይህን በዐረፍተ ነገር መጻፍ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ እንደሚረዳን በማመን የምጸናው ለምንድነው? ወይም፣ ‹‹ከእንግዲህ የያህዌን ረድኤት አልጠብቅም››