am_tn/2ki/06/30.md

1.8 KiB

ሴቲቱ ያለችውን ቃል ሲሰማ

‹‹እርሷና ሌላዋ ሴት ያደረጉትን ስትናገር ስማ››

ልብሱን ቀደደ

ንጉሡ ምን ያል እንዳዘነ ለማሳየት ከላይ የሚደርበውን መጐናጸፊያ ቀደደ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በሐዘን ልብሱን ቀደደ››

በቅጥሩ ላይ በሚመላለስበትም ጊዜ

2 ነገሥት 6፥24 ላይ ሴትየዋ ስትጠራው ንጉሡ በከተማው ግንብ ላይ እየተመላለሰ ነበር፤ አሁንም እንደዚያው እያደረገ ነው፡፡

በውስጥ ማቅ ለብሶ ነበር

ከልብሱ ውስጥ ማቅ መልበሱ ንጉሡ ምን ያህል እንዳዘነና እንደ ታወከ ያሳያል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከውጭ ከለበሰው ሥር ንጉሡ ማቅ ለብሶ ነበር›› ወይም፣ ‹‹በጣም አዝኖ ስለ ነበር ከካባው ሥር ማቅ ለብሶ ነበር››

እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ ከዚህም የባሰ ያምጣብኝ

በሰማርያ ከተማ ከሆነው የተነሣ ነቢዩ ኤልሳዕን ሳይቀጣው እንዲያውም ሳይገድለው ከቀረ እግዚአብሔር እንደሚቀጣው ንጉሡ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እግዚአብሔር ይቅጣኝ ይግደለኝ››

የሳፋጥ ልጅ የኤልሳዕ ራስ ዛሬ በዐንገቱ ላይ ካደረ

ይህ የሚያመለክተው ኤልሳዕ አንገቱ ተቆርጦ እንደሚገደል ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ዛሬ የሳፋጥ ልጅ የኤልሳዕ አንገት ሳይቆረጥ ቢቀር›› ወይም፣ ‹‹ዛሬ ወታደሮቼ የሳፍጥ ልጅ የኤልሳዕን አንገት ሳይቆርጡ ካደሩ››