am_tn/2ki/06/22.md

1.9 KiB

ኤልሳዕም መለሰ

ኤልሳዕ ለእስራኤል ንጉሥ ጥያቄ መልስ እየሰጠ ነው፡፡

ለመሆኑ በሰይፍህና በቀስትህ የማረክሃቸውን ትገድላቸው ዘንድ ይገባሃልን?

ኤልሳዕ ይህን የጠየቀው ንጉሡ እነዚህን ሰዎች እንዳይገድላቸው ለመናገር ነው፡፡ ‹‹ሰይፍ›› እና፣ ‹‹ቀስት›› በጦርነት ጊዜ ወታደሮች የሚጠቀሙባቸው መሣሪያዎች ናቸው፡፡ ይህን ዐረፍተ ነገር ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በጦርነት የያዝሃቸውን ሰዎች እንደማትገድል ሁሉ እነዚህንም ሰዎች መግደል የለብህም››

እንዲበሉና እንዲጠጡ እንጀራና ውሃ አቅርብላቸው

እዚህ ላይ፣ ‹‹እንጀራ›› በአጠቃላይ ምግብን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሚበሉትን እንጀራ፣ የሚጠጡትን ውሃ ስጣቸው››

ወደ ጌታቸውም ይሂዱ

ይህ የሚያመለክተው የሶርያን ንጉሥ ነው፡፡

ስለዚህ ንጉሡ ብዙ ምግብ አቀረበላቸው

ምግብ እንዲያቀርቡ ንጉሡ አገልጋዮቹን አዘዘ፡፡ እርሱ ራሱ ምግቡን አላዘጋጀም፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ስለዚህ ንጉሡ ብዙ ምግብ እንዲያቀርቡላቸው አገልጋዮቹን አዘዘ፡፡

አደጋ ጣዮች

‹‹እነዚያ ሰዎች››

የእስራኤልን ምድር ለመውረር ከዚያ በኃላ አልተመለሱም

ይህ ማለት ለረጅም ጊዜ እስራኤልን አላጠቁም ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የእስራኤልን ምድር ማጥቃታቸውን ለረጅም ጊዜ አቆሙ››