am_tn/2ki/06/20.md

1.3 KiB
Raw Permalink Blame History

በዚያን ጊዜ

‹‹እንዲህም ሆነ›› ወይም፣ ‹‹ያኔ›› እንዲያዩ የእነዚህን ሰዎች ዐይን ክፈት

ኤልሳዕ ሰዎቹ እንደ ገና እንዲያዩ ያህዌን ጠየቀ፡፡

አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እነዚህ ሰዎች እንዲያዩ አድርግ››

ያህዌም ዐይኖቻቸውን ከፈተ… አዩ

ያህዌ ሰዎቹ እንደ ገና እንዲያዩ ፈቀደ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ ዕውርነታቸውን አነሣ›› ወይም፣ ‹‹ያህዌ አጥርተው እንዲያዩ ፈቀደ››

እነሆ

እዚህ ላይ፣ ‹‹እነሆ›› የሚለው ባዩት ነገር ሶርያውያን መደነቃቸውን ያመለክታል፡፡

ባያቸው ጊዜ

‹‹የሶርያ ወታደሮችን ባያቸው ጊዜ››

አባቴ ሆይ

ንጉሡ ነቢዩ ኤልሳዕን እያናገረ ነው፤ አክብሮቱን ለማሳየት፣ ‹‹አባቴ›› አለው፡፡

ልግደላቸውን? ልፍጃቸውን?

እዚህ ላይ የእስራኤል ንጉሥ ስለ ወታደሮቹ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እነዚህን የጠላት ወታደሮች እንዲገድሉ ወታደሮቼን ልዘዛቸውን?