am_tn/2ki/06/10.md

1.8 KiB
Raw Permalink Blame History

የእግዚአብሔር ሰው የነገረውን ቦታ አስቃኘ

ይህ የሚያመለክተው 2 ነገሥት 6፥9 ላይ ወደዚያ እንዳይሄድ ኤልሳዕ ንጉሡን ያስጠነቀቀውን ቦታ ነው፡፡

እንደዚህ ካሉት ቦታዎች ራሱን እንዲጠብቅ ከአንድ ሁለት ጊዜ በላይ አስጠነቀቀው

አደጋው ከመምጣቱ በፊት ሕዝቡን እንዲያስጠነቅቅ፣ የሶርያ ሰራዊት የሚያጠቃበትን ቦታ ኤልሳዕ ለንጉሡ ይነግረው ነበር፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ኤልሳዕ የእስራኤልን ንጉሥ ብዙ ጊዜ በዚህ መልኩ አስጠነቀቀው፤ እስራኤላውያንም ከአደጋ ተጠበቁ››

ከእስራኤል ንጉሥ ጋር የተወዳጀ እንዳለ ለምን አትነግሩኝም?

የሶርያ ንጉሥ ለእስራኤል ንጉሥ መረጃ የሚሰጥ ሰው ወታደሮቹ መካከል ሊኖር እንደሚችል አሰበ፡፡ ያ ከሐዲ ማን እንደ ሆነ ለማወቅ ይህን ጠየቀ፡፡ ይህን በዐረፍተ ነገር ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለእስራኤል ንጉሥ እየሠራ ያለው ማን እንደ ሆነ ንገሩኝ! ወይም፣ ‹‹ዕቅዶቻችንን ለእስራኤል ንጉሥ የሚናገረው ማንኛችሁ እንደ ሆናችሁ ንገሩኝ?

ከእስራኤል ንጉሥ ጋር

ይህም ማለት ወዳጅ የሆነ ሰው ማለት ነው፡፡ እዚህ ላይ ግን ለእስራኤል ንጉሥ መረጃ የሚሰጥ ሰው ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የእስራኤልን ንጉሥ የሚረዳ›› ወይም፣ ‹‹ለእስራኤል ንጉሥ ታማኝ የሆነ››