am_tn/2ki/06/08.md

1.4 KiB

በዚህ ጊዜ የሶርያ ንጉሥ ከእስራኤል ጋር ይዋጋ ነበር

‹‹የሶርያ ንጉሥ ከእስራኤል ጋር ይዋጋ በነበረ ጊዜ››

አሁን

ይህ ቃል እዚህ ቦታ ጥቅም ላይ የዋለው የዋናውን ታሪክ ፍሰት ገታ ለማድረግ ነው፡፡ እዚህ ላይ ጸሐፊው ስለ አዲስ የታሪኩ ክፍል መናገር ይጀምራል፡፡

‹‹በዚህ በዚህ ቦታ እሰፍራለሁ›› አለ

የሶርያ ንጉሥ የት እንደሚሰፍር ለአማካሪዎቹ እየተናገረ ነበር፡፡ ‹‹በዚህ በዚህ›› የሚሉት ሐረጐች ቦታውን በጽሑፍ ባለ ማስፈር ስለ አካባቢው መረጃ የሚሰጡ ናቸው፡፡ ይህን ሐረግ በቋንቋህ በትክክል መተርጐም የማይቻል ከሆነ ቀጥተኛ ባልሆነ አነጋገር መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሚሰፍርበት ቦታ የት እንደ ሆነ ነገራቸው››

የእግዚአብሔር ሰው

‹‹የእግዚአብሔር ሰው ኤልሳዕ››

ሶርያውያን በዚያ ታች ወርደዋልና በዚያ በኩል እንዳታልፍ ተጠንቀቅ

ሶርያውያን የሰፈሩበትን ትክክለኛ ቦታ ኤልሳዕ አወቀ፤ ራሳቸውን ለአደጋ እንዳያጋልጡ የእስራኤልን ንጉሥና ወታደሮቹን አስጠነቀቀ፡፡