am_tn/2ki/04/38.md

1.2 KiB

የነቢያት ልጆች

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ እነዚህ ልጆች የነቢያት ስብስብ እንጂ፣ በቀጥታ የነቢያት ልጆች አይደለም፡፡ 2 ነገሥት 2፥3 ላይ ይህን እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡ ‹‹የነቢያት ስብስብ››

ወጥ

ብዙውን ጊዜ ይህ ማሰሮ ውስጥ የሚቀቀል የሥጋና የአትክልት ምግብ ነው፡፡

ዱር በቀል ሐረግ

ይህ አትክልት ዱር የሚበቅል ማለት ማንም ያልተከለው ነበር፡፡

በልብሱ ሙሉ ይዞ

በእጁ መያዝ ከሚችለው በላይ ብዙ የዱር ሐረግ መያዝ የሚችልበት ቦታ ለማግኘት ሲል የቀሚሱን ጠርዝ እስከ ወገቡ ድረስ አጠፈ፡፡

ምን እንደ ሆነ ግን ማንም አላወቀም

ምን ዐይነት የዱር ሐረግ እንደ ሆነ ባለማወቃቸው ለመብል መልካም መሆን አለመሆኑን አላወቁም፡፡ ይህን የበለጠ ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ነገር ግን ለመብል መልካም መሆን አለመሆኑን አላወቁም፡፡