am_tn/2ki/04/30.md

955 B

ሕያው ያህዌን በሕያው ነፍስህም

‹‹ሕያው ያህዌን፣ በሕያው ነፍስህም›› የሚለው እናትየው እየማለች እንደ ሆነ ያመለክታል፡፡ እናትየው የያህዌንና የኤልሳዕን ሕያውነት ከምትናገረው ነገር እርግጠኝነት ጋር አነጻጽራለች፡፡ ይህ መሐላ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔ እምላለሁ››

ልጁ ግን አይናገርም ወይም አይሰማም ነበር

ይህ ማለት ሕይወት አልነበረውም ማለት ነው፡፡ ይህንን ይበልጥ ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ልጁ ግን ምንም የሕይወት ምልክት አላሳየም››

ልጁ አልነቃም

እዚህ ላይ እንቅልፍ ከሞት ጋር ተመሳስሎአል፡፡ አማራጭ ትርጒም ‹‹እንደ ሞተ ነው››