am_tn/2ki/04/28.md

1.0 KiB
Raw Permalink Blame History

ጌታዬ፤ ለመሆኑ እኔ ልጅ እንድትሰጠኝ ጠይቄህ ነበርን? አጉል ተስፋ እንዳትሰጠኝ አላልሁህምን?

ሴትዮዋ ይህን የጠየቀችው በሆነው ነገር ምን ያህል እንደ ታወከች ለማሳየት ነበር፡፡ ወንድ ልጅ እንደምትወልድ በነገራት ጊዜ ከኤልሳዕ ጋር የተነጋገረችውን እየተናገረች ነው፡፡ ይህን ጥያቄ በዐረፍተ ነገር ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንዳትዋሸኝ ነገርሁህ እንጂ፣ ልጅ እንድትሰጠኝ አልጠየቅሁህም!

እንግዲህ ወገብህን ታጠቅ

‹ለጉዞ ተዘጋጅ››

ሰው ብታገኝ ሰላም አትበል፤ ማንም ሰው ሰላም ቢልህ መልስ አትስጥ

ኤልሳዕ ግያዝ በተቻለ መጠን ቶሎ እንዲሄድ፣ ከሰው ጋር ለመነጋገር መንገድ ላይ እንዳይቆም ፈልጓል፡፡