am_tn/2ki/04/12.md

1.6 KiB
Raw Permalink Blame History

ግያዝ

ይህ የሰው ስም ነው፡፡

ሱነማዪቱን ጥራት

‹‹ሰነማዪቱን ሴት ጥራት›› ይህ የሚያመለክተው ኤልሳዕ እቤቷ ይኖር የነበረውን ከሱነም የሆነችውን ሴት ነው፡፡

ለእኛ ስትይ በጣም ተቸግረሻል

‹‹በጣም ተቸግረሻል›› የሚለው አንዳች ነገር ለማድረግ ከፍ ያለ ጥረት አድርገሻል ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለእኛ ይህን ለማድረግ ትልቅ ጥረት አድርገሻል›› ወይም፣ ‹‹ለእኛ ይህን ለማድረግ ከባድ ዋጋ ከፍለሻል››

ምን እንዲደረግልሽ ትፈልጊያለሽ?

ይህን፣ ‹‹ምን እናድርግልሽ? በማለት መተርጐም ይቻላል፡፡

የምንነግርልሽ ጉዳይ አለን?

ለንጉሡ ወይም ለሰራዊቱ አዛዥ እንዲነግርላት የምትፈልገው ነገር ካለ ኤልሳዕ ሴትዮዋን እየጠየቀ ነው፡፡ ይህን ጥያቄ ግልጽ በሆነ ሁኔታ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ስለ አንቺ ጥያቄ እናቅርብ?

እኔ እኮ የምኖረው በገዛ ወገኖቼ መካከል ነው

ቤተ ሰቧ የሚያስፈልጋትን ሁሉ ስለሚያደርግላት ሴትዮዋ ምንም እንደማያስፈልጋት እየተናገረች ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በቤተ ሰቤ ተከብቤ ነው ያለሁት፤ እነርሱ ስላሉ ምንም የሚጐድለኝ የለም››