am_tn/2ki/03/24.md

1.4 KiB

የእስራኤል ሰፈር

እዚህ ላይ ‹‹እስራኤል›› የሚያመለክተው የእስራኤልን ወታደሮች እንጂ፣ ጠቅላላውን የእስራኤል ሕዝብ አይደለም፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እስራኤላውያን ድንኳኖቻቸውን ተክለው የነበረበት ቦታ››

እስራኤላውያን ወጓቸው

‹‹እስራኤላውያን›› የሚያመለክተው የእስራኤል ወታደሮችን እንጂ፣ ጠቅላላውን የእስራኤል ሕዝብ አይደለም፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የእስራኤል ወታደሮች ወጓቸው››

ከፊታቸው ሸሹ

‹‹ከፊታቸው ሮጠው አመለጡ››

ቂር ሐራሴት

ይህ የሞዓብ ዋና ከተማ ነው፡፡

ከነድንጋይዋ ቀርታ ነበር

የከተማዋ ግንቦችና ሕንጻዎች ከድንጋይ የተሠሩ ነበሩ፡፡ ይህን የበለጠ ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የድንጋይ ግንቦቿና ሕንፃዎቹ እንዳሉ ነበሩ፡፡››

ባለ ወንጭፉ

‹‹ወንጭፍ›› ከእንስሳት ቆዳ የተሠራ ረጅም ገመድ ሲሆን፣ ጫፍ ላይ ድንጋይ ወይም ሌላ ጠጣር ነገር ተደርጐለት ከሩቅ ይወነጨፍ ነበር፡፡