am_tn/2ki/03/21.md

1.5 KiB

በዚህ ጊዜ

ይህ ቃል ጥቅም ላይ የዋለው ዋናውን ታሪክ ገታ ለማድረግ ነው፡፡ የሞዓብ ሰራዊት ሦስቱን ነገሥታት ጦርነት ለመግጠም እያደረጉ ለነበረው ዝግጅት ጸሐፊው ዳራ የሚሆን መረጃ ያቀርባል፡፡

መሣሪያ መያዝ የቻለ ሁሉ

እዚህ ላይ፣ ‹‹መሣሪያ›› መዋጋት መቻል ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹መዋጋት የሚችል ሰው ሁሉ››

ነገሥታቱ… መጡ

እዚህ ላይ፣ ‹‹ነገሥታት›› ሰራዊቶቻቸውንና ነገሥታቱ ራሳቸውን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ነገሥታቱ ከሰራዊቶቻቸው ጋር መጡ›› ወይም፣ ‹‹ነገሥታቱና ሰራዊቶቻቸው መጡ››

እንደ ደም ቀልቶ ታያቸው

እዚህ ላይ ውሃው ቀይ ሆኖ መታየቱን ከደም ቀለም ጋር ያነጻጽራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንደ ደም ቀይ ሆነ››

እንግዲህ ሞዓብ

ወታደሮቹ ራሳቸውን፣ ‹‹ሞዓብ›› በማለት ነው የሚገልጹት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሞዓብ ወታደሮች››

ወደ ምርኮህ ዙር

‹‹ንብረታቸውን መዝረፍ›› ወታደሮች ጠላቶቻቸውን ካሸነፉ በኃላ ማንኛውንም ዋጋ ያለው ነገር ከከተሞቻቸው ይዘርፉ ነበር፡፡